37 thoughts on “ደቡብ – የክልልነት ጥያቄ እና ቅሬታ (ካፋ ፣ ጉራጌ ፣ ኃዲያ) – ዐቢይ ጉዳይ 24 Abiy Guday [Arts TV World]

 1. I have never been impressed like today. These three gentlemen have answered and even expressed in detail the pain of our people going beyond the line. I would especially thank Instructor Tekleab Bullo of Kaffa. He spoke my mind what I believe and of course and other of my people.
  Simply, thank you all.

 2. ብቃትና ብቃት ያለው ጋዜጣኛ አቶ መላኩ! የት ነበርክ እስከ ዛሬ? ኦሎፔምያ እንዳትለኝ

 3. ጉራጌ ድሮም የእራሱ ግዛት ነበረው ወያኔ ነው ወስዶ ከድቡብ ጋ እየተጨፈለቀ ያለው አሁንም የእራሱ ክልል ሊኖርው ይገባል እስከ አዋሽ ወሊሶ ሰበታ ድረስ የጉራጌ ግዛት ነው በታሪክ ተቀምጧል

 4. ከሶስት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በብሄራቸው በተፈናቀሉባት አገር ከብሂረተኝነትና በራስ ክልል ከመደራጀት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም እያሉን ናቸው። ጉራጌ በጉራጌነቱ ከየትም ተፈናቅሎ አያውቅም ይለናል ደፋሩ ፖለቲከኛ። ሁሉም የሚሉት የኛ ብሄር አያፈናቅልም ነው። ልጆቹ ነፍ ውሸት እየለቀቁብን ናቸው። እንደነሱ አባባል ኢትዮጵያ ሰማንያ አራት ክልል ይኖራታል፣ ሁሉም ክልልሎች የድንበር ጦርነት ውስጥ ይማገዳሉ ማለት ነው። የነዚህ ልጆች የፖለቲካ አግጣጫ በወያኔ የተተለመው ነው። በተለይ የጉራጌ ፓርቲ መሪ ነኝ የሚለው ልጅ ዘር ተኮርና አደገኛ አቅጣጫ የያዘ ብቻ ሳይሆን ሃሳቦቹ በጣም ግልብና ጥልቀት የሌላቸው ናቸው። እንኩዋንም ይሄንን አየሁ። ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ አደገኛ መሆኑን ያሳያል።

 5. እነዚህ ወጣት ፖለቲከኞች የወያኔን ህገመንግስት እንደሃይማኖት የሚያምኑበት ነገር በመሆኑ ይሄንን ህገመንግስት የማሻሻል ወይም የመቀየር ተስፋችን የመነመነ መሆኑን ዛሬ ተረዳሁ።

 6. ወጣቶቹ በጣም የነቁና የሚናገሩትን የሚያውቁ ናቸው። እስካሁን ግን ክልል እንሁን ከሚለው መፈክር ያለፈ ራእያቸውን አላካፈሉንም። ሃምሳ ስድስት ክልል ያዋጣል ወይ፧

 7. እንግዶቹ በሙሉ ያስተናጋጁ ታናናሾች ሆነው ለምን በ አንቱታ እንደሚጠራቸው አልገባኝም። እነዚህ ፖለቲከኞች ናቸው እንጂ ከፍተኛ ያመንግስት ባለስልጣኖች አይደሉም። ይ አማርኛው አገባብ፣ "አንቱታ" በእድሜ ለታላቅ፣ አዛውንት እኩያሞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ታላላቅ የአገር መሪዎች….ነው። ሌላው ነገር፣ ፖለቲከኞቹ እንግሊዘኛ የሚይበዙት ለምንድን ነው፧ ብዙዎቻችን ጉራጌዎች፣ ሃዲያዎች እና ቦንጋዎች እንግሊዝኛ አንናገርም። እንግሊዝኛ እንደሚናገሩ ካልታወቀ ምናልባት ተከታይ አያገኙ ይሆን እንዴ፧

 8. Lemin zone yemilewun mewakir askeritew kilil ayiluachewum. Simun aydel ends yemifelegew. Keza budjet ends population sizachew mestet new. Yemin shirgud new hulum ethiopiawi new. Anfeligim erasachinin erasachin enmeralen malet bezih gize mebt meselegn. Likekuachew mebtachewun atigedibu….. Midre dedeboch

 9. ደቡብ እንዲህ ብስል ስክን ያሉ ወጣት ልሂቃን ካሉት ኢትዮጵያን መታደግ ይችላል። ይደመጡ ! አማርኛቸው ራሱ አንዳንዴ ካልሆነ በቀር ጥርት ያለ፤ ተናገርኩ ብሎ ከባህርዳር ወይ ከአዲሳባ ለሚመጣው ምሑር በሉኝ ዶ/ር መቶ በመቶ ይሻላል፤ ይመስጣል።

 10. የተጨቆነው ህዝብ ፈርጦች፣ጀግኖች በርቱ
  ኢ/ር ሸዋለም የአያቶችህ የነ ፊት አውራሪ ኡመር ፋርዳ፣የነ ፊት አውራሪ ላማደ ቱፋ ….ወዘተ ዘር ልበ-ሙሉ

 11. Bravo kaffa, gurage and hadya. You need to claim your history and heritage just like sidama. Ignorant woyanne tried to destroy your autonomy and history giving you a region named with direction while they scream false biher bihereseboch.

 12. በድንቅ ተንታኝ ተክለአብ በሃገራችን በጣም ኮርቻለሁ:: የብሄር የጎሳ ካባ ሃገር ሳያጠፋ በፊት ሃገራዊ የክልል ምስረታ በጥናት ይካሄድ:: ከፋም ሲዳሞም ገሙም ትግሬም ድሮ ክፍለሃገር ጠቅላይ ግዛት ነበሩ:: ነገሩ ሁሉን በሚያቅፍ በሚዛናዊ መንገድ መፈታት ይኖርበታል:: ሲዳማዎችን በሰላም ካልሆነ በሃይል ክልል መሆን ይኖርባቸዋክል በማለት ለዘር ማጥፋት ግድያዎቹ ቀስቃሽ ጃዋር መሀመድ ለፍርድ መቅረብ ይኖርበታል::

 13. Tekleab !!! You are our hero. I have no words to say about your reasons and presentations for keffa peoples and their struggle to see new Ethiopia, but that way strictly hurt the keffa peoples and make them not able to lead them selves and use their resource wisely.So know is the time to make keffa peoples great with the help of Almighty God.
  Tekleab your are Logical, Respectful and all of your words were based on constitutional Arena and all of the keffa Gurmasho including me are with you .

 14. This Bright minded youngsters I am impressed with, but it is sad to see they are forced to use their talent and there prime time with this nonsense ”kelele” BS.
  We need to discuss more on food security, technology and how to build the 21st century Ethiopia and Ethiopiawent.

 15. እነዚ ወጣቶች በጣም በሳልና አስተዋዬች ናቸው :: በፖለቲካ በስለናል የሚሉት ከኔ ክልል ያሉ የአማራ አክቲቪስት ተብዬዎችን ብሎም በፖለቲካ እኛን የሚያክል የለም እያሉ የሚመፃደቁብንን የኦሮሞ , የትግራይ , የአማራ , አክቲቪስት በሙሉ በአንድ ላይ ቢጭፈለቁ እነዚህን 3 አንበሶች አያክሉም እነዚህ ይብሏቸዋል :: አቦ በርቱ

 16. ጥያቄው ግን እነዚህ ሰወች United States of America ወይንም Europian Union ሲባል ሰምተው አያውቁ ይሆን? በአውሮፓ ህብረት በሚል የጋራ ህብረት ፈጥረው ዛሬ ዜጎቻቸው በፈለጉት አገር መኖትና መስራት እንዲችሉ አድርገዋል, በመካከላቸው ያለው ድንበር መስመር ብቻ ሆኗል, ንግዱም ጦፏል የድንበር ቁጥጥር ስለለ, ዜጎቻቸው ከአንዱ አገር ወደ ሌላው አገር ለመጏዝ መታወቂያ በመያዝ መኪናቸውን ይዘው ወይንም በባቡር ተሳፍረው መጏዝ ነው, ወደ አውሮፓ የሚጏዙ ቱሪስቶችም የአንዱን አገር ቪዛ ካስመቱ ገንዘቡ ካላቸው በዚህ ቪዛ ሁሉንም አባል ሀገሮች መጎብኘት ይችላሉ, ዜጎቻቸው በጉዞ ላይ እንዳሉ ቢታመሙ የህክምና ኢንሹራንሳቸውን ካርድ በአባል ሀገሮች በመጠቅም ሊታከሙ ይችላሉ, ወዘተ.
  የኛ አገር ደግሞ ሁሉም ክልል እያለ በበረት ውስጥ ለመኖር ሲጥር ማየት በጣም ያሳፍራል! ክልል ማለት ግቢ ወይንም በረት ማለት ነው. ይህ ክልል የሚባል ነገር ዛሬ ለሁሉም ቢሰጥ ነገ የህዝቡ ቁጥር ሲጨምርና ዛሬ የእርሻ ቦታ ዩሆነው ነገ የመኖሪያ ቦታ ስለሚሆን ሁሉም ክልሎች ክልላቸውን ማስፋት ስለሚፈልጉ የእርስ በእርስ ግጭት ያመጣሉ በመካከላቸው ግንብ እስካልተገነባ ድረስ!
  በሰለጠኑ አገሮች የተለያዩ የዱር አውሬወችን በተለይ ከአፍሪቃ ያመጡና ለብቻ ለብቻ ከልለው ያኖሯቸዋል ልክ እኛ አገር ክልል እንደሚባለው. ይህን የሚያደርጉት አንበሳውን ከሜዳ አህያው ጋር አብረው ቢያደርጉት አንበሳው የሜዳ አህያውን ስለሚበላው ነው. በመካከላቸው አጥር አድርገው ቱሪስቶች የመግቢያ ዋጋ እየከፈሉ በመዘዋወር እነዚህን የዱር አራዊቶች ይጎበኛሉ የግድ አፍሪቃ ድረስ ተጉዘው አውሬወችን ማየት የለባቸው.
  እራሳችንን ከሌላው አለም ህዝብ ጋር እስካላወዳደርን ድረስ ገና ብዙ ችግሮች እንሰማለን! አሁን እኮ ከአውሮፓ, ከአሜሪካና ከኤስያ አገሮ ዜጎች ጋር እራሳችንን ልናወዳድር ቀርቶ ከጎረቤት የአፍሪቃ አገሮች ጋር ማወዳደር ተስኖናል! ጎረቤት ኤርትራ 9 ብሄሮች, ጎረቤት ሱዳን 600 ብሄሮች, ደቡብ ሱዳን 60 ብሄሮች, ጂቡቲ 2 ብሄሮች, ወዘተ አብረው በሰላም እየኖሩ እኛ ግን ለመበታተን መከራችን እናያለን!
  አይናችንን ከፈት አድርገን ሌላውን አለም ማየት አለብን!

 17. እግዚአብሔር ይባርካችሁ በርቱ ይናንተ ነጥብ በጣም የሚደነቅ ነው ወይ ክልል ይቅር ወይም ለሁሉም ይሰጠው በሚለው እስማማለሁ ልክ ብዙዎቹ እንዳሉት ጉራጌዎቹ ሀገር እያለሙ በገዛ ሀገራቸው መጤ ሲባሉ እና ሲዘረፋ ትንሽ ያሳዝናል ስለዚህ እነዚህ ስራ የሚወዱ ህዝቦች የራሳቸው ክልል ቢኖራቸው እኛ ወደነሱ የምንሰደድበት ሀገር እንደሚያደርጉት ጥርጥር የለውም

 18. It was this kind of time Hitler brainwashed Germany people and sent them to second world war ejeto kero and fano is trying to do the same please think twice before you follow this the so called leaders follow Abiy

 19. Wegenoch sijemer Weyane ina Oneg yeserut tenkol. Lenesu endimechachew bicha ahadawi sireat ayasfeligim belew bekuankua Tigrayin ina Oromian kehulum tekeramtew tekafelu ina keza Amara kilil yalutin yenifeligutin yahil meret zerfew, liyu zone yemibal neger endiset aderegu, keza debubin degmo still beAhdawi wust endenesu Ababal cheflikew askemetut. Betam yemigermegne new. Yemayafru.

 20. ከጠያቂዉ ጀምሮ ሑላችሑም በጣም ደስ የሚል ዲስከሽን ነው የምታደርጉት እግዚአብሔር ይርዳችሁ ፍትሕ ለተጨቆነ ሕዝብ .እኔን እየገረመኝ ያለው የሌላው ዝምታ ነው በተለይ ደሞ የጉራጌ ሕዝብ ፖለቲካን ጥላቻ ዝም ማለት ሐገር እስክናጣ ነው ወይ ዝምታችን እኛ ጉራጌዎች ማንም ጠላት የለንም ከሌላው ጋር ለመፎካከርም አይደለም ግን ጉራጌ ዝምታን በመምረጡ በኢኮኖሚውም በሑሉም ነገር በጣም ነው የተጎዳው እስከመቼ ነው በሙስና ሣይሖን በላቡ ያፈራዉን እየተዘረፈ እየተፈናቀለ የሚኖረው የጉራጌ ዞን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሔደ ጊዜ ማደሪያ ሖቴል እንኳን ነው ያጣው እያዋጡ ትምህርት ቤት ሖስፒታል ብዙ ነገር ማድረግ ሢችል ከ20 አመት በፊት የሕዝብ ቁጥር ከዎሮሞና ከአማራው ቀጥሎ ጉራጌ ከ7 ሚሊየን በላይ ነበር ትግሬ 6ሚሊየን ነበር ቢያንስ አሑን የጉራጌ ሕዝብ ከ15 ሚሊየን በላይ መሖን ሲኖርበት እንዴት ሖኖ ነው ከ3 ሚሊየን ያነሠ የሚሖነዉ በዙ የተማረ አለ ዝምታዉ ይብቃ የሐገርን ሠላም በጠበቀ መልኩ ለሚካሔደው ነገር አስተዉፆ ማድረግ ይጠበቅብናል እንደዚህ ስል የከፋዉም የሐዲያዉንም ወንድሞቼ ፍትሕ ለሑላችንም እኩል ነው እንጂ እየተነጠለ መሖን የለበትም ግን ጉራጌው ከብዛቱ ምንም እንቅስቃሴ ዉስጥ ሥለማይገባ ገርሞኝ ነው ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በፖለቲካ ከሚንቀሳቀሱት በላይ ዝም ያለው ሕብረተሰብ ይበዛል ጠቅላይ ሚኒሥተር ዶክተር አብያችን እንደተናገሩት

 21. ለሢዳማ ክልልነት ከተፈቀደላቸው ለሑሉም መሖን አለበት እንጂ እንደገና ሌላዉ የሚጨፈለቅበት አንድም ምክንያት የለም ዜጋ ዜጋ ነው እንጂ አንዱ አንደኛ ዜጋ ሌላው ሑለተኛ በታምር መሖን የለበትም የሢዳማ ጥያቄ የቆየም ይሑን የትላንት አይደለም ጥያቄው በደቡብ ክልል ዉሥጥ ነው የኖረው ሐዋሣ የለማችዉ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ስለሖነ የነሡ ጥያቄ ይመለሣል ከተባለ ለሑሉም እኩል ነው መሖን ያለበት እንጂ እንደገና ሌላውን በታምር መጨፍለቅ የለበትም በጠቅላይ ሚኒሥተር ዶክተር አብይ ትልቅ እምነት አለን ሑሉንም ፌር በሖነ መንገድ መሠጠት አለበት ወይንም ሐገር እስክትረጋጋ ሲዳማዉም ሑሉም በትእግስት ቆይቶ እንደገና መዋቀር አለበት

 22. THANK YOU ART RV FOR BEING VOICE TO VOICELESS PEOPEAL .THE PAST 27 YEARS SEDAMA PEOPEAL ARE rain THE SOUTH SO NO MORE POWER CONTROL ONLY BY SEDAM PEOPEAL. WE HAVE TO FIGHT BACK THOSE 👹👺 THE GURAGE,KEFAA WE HAVE BEEN HAVING OUR REAGAN FOR LONG TIME THE WAYANN THEY DEMOLISHED ALL THIS

 23. ከፍ የቡና መገኛ ለከፋ ምድር ምንም አስተዋፆ ሳያረጉ የመሬታችንን ተቀራምተው የበይ ተመልካች የሆነች አገረ

 24. ስለ ከፍ በጣም ታሬክ አዋቄዋች አሉ ከፍ በራሱ በንጉሱ ስርአት ሲተዳዳር የነበረ የራሱ ባህል ያለው ህዝብ ነው

 25. ATO TEKLE AB YANESA HASAB TIKEKEL NEW. BE KILEL YETEDERAJU HULUM KILELOCH YIFRESUNA ENDEGENA ADDIS ASTEDADER YIMESRET

 26. ደህዴግ በህወሃት ተጠፍጥፎ የተሰራ የጥቂት አምባገነን ግለሰቦች ስብስብ ነዉ :: በጣም ኢ-ዲሞክራሲያዊ ከመሆኑ የተነሳ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችን በድሞክራሲ ለመመለስ ሞራሉም ሆነ ብቃቱ የለውም::

 27. በጣም ጠቃሚ የሆነ discussion ነዉ:: ይህ መሰረታዊ የሆነ ህገመንግስታዊ ክልል የመሆን ጥያቂዎች በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት በቶሎ በአግባቡ መመለስ አሰፈላጊ ነዉ:: አላስፈላጊ የሰው ሕይወት እና የንብረት መውደም መከላከል የመንግስት ኃላፊነት ነዉ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *